Fana: At a Speed of Life!

የሐዋሳ ሀይቅን የማስዋብ ፕሮጀክት አካል የሆነው አካባቢውን ነጻ የማድረግ ሥራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐዋሳ ሀይቅን የማስዋብ ፕሮጀክት አካል የሆነው አካባቢውን ነጻ የማድረግ ሥራ መጀመሩን ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
በከተማዋ በ2014 ከሀይቁ ማስዋብ ጋር በተያያዘ በይፋ ከሚጀመሩ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የሐዋሳ ሀይቅ የማስዋብ ስራ ነው ዛሬ የተጀመረው።
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም የሐዋሳን ሀይቅ ለዘርፈ ብዙ የቱሪዝም መስህብነት ብቁ ያደርገዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከሐዋሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.