Fana: At a Speed of Life!

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ከተማዋ ሊገባ የነበረ 49 ሺህ 300 ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ከተማዋ ሊገባ የነበረ 49 ሺህ 300 ዶላር በቁጥጥር ስር ዋለ።

በኮምቦልቻ ከተማ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ኬላ ኮድ3 የሰሌዳ ቁጥር 89654 የሆነ መኪና መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ወደ ኮምቦልቻ ሊገባ ሲል በብሔራዊ ደኅንነት፣ በፓሊስ እና ኬላ  በሚጠብቁ ወጣቶች ትብብር በቁጥጥር ሥር መዋሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የታክቲክና ወንጀል ምርመራ ክፍል ኀላፊ ኮማንደር አሊ ሰይድ ገልጸዋል።

እንደ ኮማንደር አሊ ገለጻ ከምሽቱ 2:40 ሰዓት ላይ ተጠርጣሪው አሽከርካሪ በኬላው ላይ በነበረ ፍተሻ ከነ ዶላሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

ወጣቶች በኬላ ፍተሻ እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ የሚበረታታ መሆኑን የገለጹት ኮማንደር አሊ ወጣቶች እየሠሩ ያሉትን አካባቢን በንቃት የመከታተል ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

በኬላ ጥበቃ ላይ አሚኮ ያነጋገረው በጎ ፈቃደኛ ወጣት ሐሰን እንድሪስ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመቅበር በግንባር ከሚደረገው ትግል ባለፈ አካባቢን የመጠበቅ ሥራ እያከናወኑ እንደሚገኝ  አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.