Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሂሩት ከብራሰልስ የዲፕሎማቲክ የትምህርት ተቋም ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂዬም የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ከብራሰልስ የምርምር ማዕከል የዲፕሎማቲክ የትምህርት ተቋም ፕሬዚዳንት አምባሳደር ጃን ዲ ቦክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል በሚደረጉ ትብብሮችን ዙሪያ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በተለይም የምርምር ማዕከሉ ከኢትዮጵያ መሰል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የትብብር ግንኙነት መመስረት የሚችልበት ሁኔታ ላይ በትኩረት መወያየታቸው ተገልጿል።
ተቋሙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ትምህርታቸውን የተከታተሉበት ሲሆን÷ ከ40 በላይ ሀገራት የመጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.