Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ ወጣቶች በማይጠምሪ ግንባር ለተሰለፈው ሃይል ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ደጀን ለ ኢትዮጵያ” በሚል ንቅናቄ የጎንደር ከተማ ወጣቶች በማይጠምሪ ግንባር ለተሰለፈው ሃይል ማዕድ አጋሩ፡፡
በጎ ፍቃደኛ ወጣቶቹ ከከተማው ማህበረሰብ ያሰባሰቡትን ማዕድ ፣ የተለያዩ አልባሳትንና የንፅህና መጠበቂያዎችን ነው ድጋፍ ያደረጉት ፡፡
በስነ-ስርዓቱ ላይ ከተገኙት የመከላከያ ሰራዊቱ መካከል ሻለቃ ስንቁ ሲሳይ እንደተናገሩት ህዝባችን እስከ ግንባር ድረስ በመምጣት እያደረገ ያለው ድጋፍና እገዛ ፣ ዝግጁነታችንን ይበልጥ አጠናክረን የጀመርነውን የህልውና ዘመቻ በድል ለመፈፀም ትልቅ እገዛ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
የአማራ ልዩ ሃይል አመራር ሻለቃ ስዩም ተገኝ የሽብርተኛው ሃይል ግብዓተ-መሬት ለማፋጠን ደጀን የሆነው ህዝብ ሁለንተናዊ አለኝታነት ትልቅ የሞራል ስንቅ በመሆኑ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የደጀን ለኢትዮጵያ ማህበር አባላት ህይወቴን ለአገሬ ፤ ደሜን ለህዝቤ ብሎ መስዋዕትነት እየከፈለ ጠላታችንን በመደምሰስ ላይ ለሚገኘው ሀይላችን ደጀን ለመሆን በበጎፍቃደኝነት እንደተሰለፉ ገልፀው ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማስታወቃቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.