Fana: At a Speed of Life!

የዴልታ ኮቪድ ታካሚዎች በእጥፍ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል – ጥናት

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሪታንያ በስፋት ተሰራጭቶ ከነበረው የአልፋ ኮቪድ19 ቫይረስ ይልቅ በዴልታ ኮቪድ የታመሙ ታካሚዎች በእጥፍ እንክብካቤ እንደሚሹ በእንግሊዝ የተሰበሰበ መረጃ አመላከተ፡፡

ጥናቱ እንዳመላከተው አዲሱ ዴልታ ኮቪድ ከበድ ያለና ከዚህ በፊት ከነበረው የቫይረስ አይነት ይልቅ ሁለት እጥፍ የህክምና ክትትልን የሚሻ ነው።

የኮቪድ19 ክትባት በቫይረሱ ምክንያት የሚደርስ ከፍተኛ ሕመምን እንደሚቀንስ የጠቀሰው ጥናቱ፥ በዴልታ ምክንያት የሚከሰተው የኮቪድ19 ሕመም ግን ትኩረት የሚፈልግ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የዴልታ ኮቪድ19 ቫይረስ በመላ ብሪታንያ እንደተሰራጨም ነው የተመላከተው፡፡

በእንግሊዝ የሕብረተሰብ ጤና እና ሜዲካል ጥናት ምክር ቤት የተመራው ይህ ጥናት እንዳመላከተው፥ በመጋቢት እና ሚያዝያ ወር በ43 ሺህ 338 ሰዎች ላይ ኮቪድ19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ሕመምተኞቹም ምንም አይነት ክትባት እንዳልወሰዱ የተረጋገጠ ሲሆን÷ ከታማሚዎቹ ውስጥ አብዛኛዎቹ የሆስፒታል ህክምና ክትትል እንዳላስፈለጋቸውም በጥናቱ ተጠቅሷል።

ይሁን እንጅ የዴልታ ቫይረስ የተገኘባቸው 2 ነጥብ 3 በመቶ እንዲሁም አልፋ ቫይረስ የተገኘባቸው 2 ነጥብ 2 በመቶ ያህሉ ግን ተጨማሪ የሆስፒታል የህክምና ክትትል አስፈልጓቸዋልም ነው ያለው።

ጥናቱ መከተብ በሁለቱም የኮቪድ ዝርያዎች የሚከሰተውን አደጋ እንደሚቀንስ ማመላከቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.