Fana: At a Speed of Life!

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 354 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በልዩ ልዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 354 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ይህ ለ3ኛ ጊዜ እንደሆነም ነው የተመላከተው፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱም ላይ የኦሮሚያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የዩኒቨርሲው የቦርድ ሠብሳቢ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ መገኘታቸው ታውቋል፡፡

ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ÷ ተመራቂዎች ያስተማራቸውን ማሕበረሰብ በሃቅ እና በታማኝነት እንዲያገለግሉ መልዕክት ማስተላለፋቸው ተገልጿል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ሙክታር ሙሐመድ በበኩላቸው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈው÷ ዩኒቨርሲቲው የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት ለሀገር ግንባታ የበኩሉን እያበረከተ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ለተመራቂዎችም መልካም ዕድል እንዲገጥማቸውና ያስተማራቸውን ማሕበረሰብ በታማኝነት እንዲያገለግሉ ነው ያሳሰቡት፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሕብረተሰብ ሳይንስ እና በመሬት አስተዳደር ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት ኮሌጆቹም ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳስመረቀ ነው የተመላከተው፡፡

ከተመራቂዎችም 38 በመቶ ያህሉ ሴቶች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ከተመራቂ ቤተሰቦች በተጨማሪ የፌዴራል፣ የወረዳ እና የአካባቢው ባለስልጣናት እንደተገኙ ታውቋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በበኩላቸው÷ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የ4ኛው ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚባሉት አንዱ መሆኑን ገልፀው በቴክኖሎጂ ዘርፍ እያበረከተ ያለው ሚና የሚያስመስግን እና ተስፋ ሰጪ መሆኑን መግለፃቸውንም የኦቢኤን ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.