Fana: At a Speed of Life!

ፌዴሬሽኑ በአረንጓዴ አሻራ የንቅናቄ መርሃ ግብር ላይ ተሳተፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በግብርና ሚኒስቴር በተጠራው “ኑ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል የሚከናወን የንቅናቄ መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተሳታፊ ሆኗል፡፡

በፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የተመራው የስራ አስፈፃሚና ማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት፣ እንዲሁም ታዋቂ አትሌቶችና አሰልጣኞችን የያዘ ልኡክ በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋወር ንቅናቄ የመፍጠር ተግባራት አከናውኗል፡፡

ፌዴሬሽኑም በነገው ዕለት በሚካሄደው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፍ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.