Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ኡጋንዳ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኡጋንዳ ቆይታቸውም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉዳዩን አስመልክቶ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ ÷ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል እና በበርካታ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ላደረጉት ውይይት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.