Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ያለምዘርፍ በሴቶች ግማሽ ማራቶን ሩጫ ክበረ ወሰን ሰበረች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በአየርላንድ አንትሪም ኮስት በተካሄደው የሴቶች ግማሽ ማራቶን ሩጫ የዓለም ክበረ ወሰን ሰብራለች።
 
አትሌት ያለምዘርፍ 1:03.43 በሆነ ሰዓት በመግባት ነው የርቀቱን ክብረ ወሰን መያዝ ያቻለችው፡፡
 
በዚህም ከዚህ በፊት በኬኒያዊቷ አትሌት ሩት ቼፕንጌቲች ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ19 ሰከንዶች ማሻሻል መቻሏ ተመላክቷል፡፡
 
በተመሳሳይ በወንዶች የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ጀማል ይመር 1 : 29 በሆነ ሰዓት በመግባት ማሸነፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.