Fana: At a Speed of Life!

የባንኩ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት 500 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር ለሚዋደቀው መከላከያ ሠራዊት፣ ለልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ከ500 ሚሊየን ብር በላይ ለግሰዋል፡፡
 
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ባንኩ ከዚህ ቀደም 300 ሚሊየን ብር ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።
 
በዛሬውም ዕለት ደግሞ የባንኩ ሠራተኞችና የማኔጅመንት አባላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን በድምሩ ከ500 ሚሊየን ብር በላይ መለገሳቸውን ገልጸዋል።
 
ድጋፉም ለመከላከያ ሠራዊትና ለክልል ልዩ ኃይሎች እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት ችግር ላይ ለወደቁ የማኅበረሰበ ክፍሎች የሚውል ነው ብለዋል።
 
ግንባር ለመሄድ ለወሰኑ የባንኩ ሠራተኞችም ባንኩ ደሞዛቸውንና ጥቅማጥቅማቸው እንዲከበርና ለቤተሰቦቻቸው አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ውሳኔ መተላለፉን ተናግረዋል።
 
እስካሁንም አራት የባንኩ ሠራተኞቹ ወደ ግንባር መሄዳቸውን ነው የጠቆሙት።
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ኃብት 1 ነጥብ 1 ትሪሊየን ብር መድረሱን ገልጸው÷ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ካሉ ባንኮች መካከል ትሪሊየን ኃብት በመፍጠር ሁለተኛው ባንክ መሆኑን አንስተዋል።
 
የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባንኩ ከ140 ቢሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ የቻለበት ዓመት እንደነበርም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.