Fana: At a Speed of Life!

በ35 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የማጂ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል መንግስት ድጋፍ በ35 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የማጂ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታው ተጠናቆ ተመርቋል።
 
ሆስፒታሉ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካ እና የኦሞ ፖርክ ሰራተኞችን ጨምሮ በአካባቢው ለሚገኙ ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
 
የሆስፒታሉ መመረቅ ከዚህ በፊት የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት የሚያስቀር መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
 
በ2003 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠለት ሆስፒታሉ የነበረበት የግንባታ መጓተት ችግር ተፈቶ መጠናቀቁን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ መራሃኝ በላይ ገልጸዋል።
 
ሆስፒታሉ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ቢጀምርም የህክምና ቁሳቁሶች ገና ያልተሟሉለት በመሆኑ ልዩ ትኩረት እንደሚያስፈልገው ጠቁመዋል።
 
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ናፍቆት ብርሃ በበኩላቸው÷የማጂ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያለበትን የቁሳቁስ ችግር ለመፍታት ክልሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
 
በተስፋየ መሬሳ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.