Fana: At a Speed of Life!

አመራሩ ከወጣቱ ጋር ተቀራርቦ በመስራት ወቅቱን የሚመጥን አመራር መስጠት አለበት-ዶ/ር አህመዲን

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አመራሩ ከወጣቱ ጋር ተቀራርቦ በመስራት ወቅቱን የሚመጥን አመራር መስጠት እንዳለበት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አህመዲን መሐመድ ገለጹ፡፡
የደብረ ብርሃን ከተማ ወጣቶች “ከአባቶታችን የተረከብነውን ‘ታሪክና ማንነት’ በደምና አጥንታችን አስጠብቀን ለትውልድ እናስረክባለን!” በሚል መሪ ሃሳብ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል፡፡
በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አህመዲን መሐመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የሸዋ ማህበራት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
በውይይት መድረኩ የተጀመረውን የህልውና ትግል በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡
አመራሩ ከወጣቱ ጋር ተቀራርቦ በመስራት ወቅቱን የሚመጥን አመራር መስጠት እንዳለበት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን ተናግረዋል፡፡
የሚያጋጥሙ ችግሮችን በስክነት መፍታት አስፈላጊ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ዴኤታው÷ የጠላትን ዓላማ፣ አጀንዳና ስትራቴጂ አውቆና ተንትኖ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ጦርነት ይዞት የሚመጣውን የኢኮኖሚ ጫና ለማስቀረትም ጎን ለጎን የልማት ስራዎችን መስራት እና የዘማች ቤተሰቦችን ማገዝ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በተለይ ወጣቶች አሁን ያሏቸውን ጥያቄዎች ሁሉ ወደ ጎን በመተው በዚህ የህልውና ትግል ወቅት ከሀገራቸውና ህዝባቸው ጎን መሰለፍ እንዳለባቸው መግባባት ላይ መደረሱንም በማህበራዊ ስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.