Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ባለሃብቶች በማይጠብሪ ግንባር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ባለሃብቶች በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኙት የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ 1ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የአልባሳት እና የለስላሳ መጠጦች ድጋፍ አደረጉ፡፡
ድጋፉ 150 ደርዘን የለስላሳ መጠጥ ፣ 150 የውሀ ኮዳ እና 1 ሺህ 500 ካናቴራ ነው ።
የባለሀብቶቹ ተወካይ አቶ ሙሉጌታ ቢያዝን፥ ድጋፉ በሀገር ውስጥ ባሉ የአማራ ባለሀብቶች ብቻ የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀዋል።
በቀጣይ በውጪ ሀገር ከሚኖሩ ባለሀብቶች ጋር በመቀናጀት አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሙሉ በሙሉ እስከሚደመሰስ ድረስ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የምዕራብ ዕዝ ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል የሎጅስቲክ አስተባባሪ ሻለቃ ጉልላት ነጋሽ፥ በአማራ ክልል የሚገኙ ባለ ሀብቶች ለፀጥታ ሃይሉ ላደረጉት ድጋፍ ማመስገናቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
93,669
People Reached
4,273
Engagements
Boost Post
2.1K
52 Comments
48 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.