Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ተገቢ ያልሆነ ጫና እና ጭማሪ በሚያደርጉ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ተገቢ ያልሆነ ጫና እና የክፍያ ጭማሪ የሚፈጽሙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው ባወጣው መግለጫ የግል ትምህርት ተቋማቱ የትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ እና የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን አስታውሷል።
እንዲሁም የኮቪድ19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የተቀመጠውን ፕሮቶኮል በማክበር የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዲከናወን ማድረጋቸውን ጠቅሶ፥ ላደረጉት ስራ እውቅና እንደሚሰጥ ገልጿል።
ከዚህ ባለፈም ማህበራዊ ተሳትፎ በማድረግ ሃላፊነታቸውን መወጣታቸውንም ጠቁሟል።
ይሁን እንጂ ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለትምህርት አገልግሎት እና ምዝገባ ከወጣው ማስፈጸሚያ ውጭ በርካታ ትምህርት ቤቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ነው ያለው።
ለቢሮው እና ለወላጅ ምላሽ በመስጠታቸው እና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰዳቸው በ41 የትምህርት ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ እንዲነሳላቸው እና አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉንም አውስቷል።
ኢትዮጵያዊ የጨዋነትና የአብሮነት እሴቶችን በማዳበር ይህን ወሳኝና አስቸጋሪ ጊዜ በጋራ ማለፍን ማዕከል በማድረግ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ሚና እንዲወጣም ጥሪውን አቅርቧል።
በቀጣይም ከመመሪያው ውጭ ተገቢ ያልሆነ ጫና እና የክፍያ ጭማሪ በሚፈጽሙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of text that says 'አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ BIIROO BARNOOTA BULCHINSA MAGAALAA FINFINNEE ADDIS ABABA CITY ADMINISTRATION EDUCATION BUREAU'
38,441
People Reached
1,670
Engagements

-1.3x Average

Distribution Score
Boost Post
879
50 Comments
64 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.