Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰን ለሰበረችው አትሌት ያለምዘርፍ የእንኳን ደስ አለሽ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዓለም ግማሽ ማራቶን ክብረወሰንን ለሰበረችው አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የእንኳን ደስ ያለሽ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የኢትዮጵያ ልጅ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በሴቶች ግማሽ ማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት በመሆኗ ኮርተናል፤እንኳን ደስ ያለሽ”ብለዋል።

“እንዲህ በተግባር የሚታይ ልዩ ብቃት የሀገርን ልዕልናን ከፍ አድርጎ ስለሚያንጸባርቅ ሁሌም ይወደሳል!” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፋት መልዕክት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.