Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልልትምህርት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ከክልል ፣ ከዞኖች፣ ከልዩ ወረዳዎች እና ወረዳዎች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር በቡታጀራ ከተማ ተወያይቷል።
ውይይቱ በትምህርት ዘርፍ አበይት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።
ውይይቱ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ያከናወናቸውን ተግባራት በመገምገም ለ2014 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ ባለድርሻ አካላትን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ከዚህ ባለፈም የኮቪድ19 ወረርሽኝን በመከላከል የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑም ነው የተገለጸው።
ባለፉት አመታት በክልሉ በየደረጃው ህብረተሰቡን በሚፈለገው ደረጃ በማሳተፍ የትምህርት ጥራትን፣ ተገቢነትንና ፍትሃዊነትን ለማሳደግ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል ተብሏል።
በትምህርት ተደራሽነትና ተሳትፎ፣ ውስጣዊ ብቃት፣ ጥራትና ፍትሐዊነት እንዲሁም በተማሪዎች የመማር ውጤትና ስነ ምግባር ላይ አዎንታዊ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏልም ነው የተባለው።
በአንጻሩ የትምህርት ጥራትና ተገቢነት እንዲሁም ፍትሃዊ የትምህርት አቅርቦትን ከማሳደግ አንጻር ውስንነቶች እንዳሉ ተገምግሟል፡፡
የኮቪድ19 ባስከተለው ጫና ምክንያት የተሟላ ተማሪ ወደ ትምህርት ስርዓቱ ማምጣት ባለመቻሉ ከ300 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ቀርተዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው ባለድርሻ አካላትም ‘‘ስለ ልጆቻችን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚመክር መድረክ በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ሰጥተነዋል ያሉ ሲሆን÷ በቁርጠኝንት ለመስራትም ቃል ገብተዋል።
በዑስማን መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.