Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ለማዳንና የብልፅግናን ትልም ለማሳካት ትምህርትና እውቀት ዋነኛ መሳሪያ ነው-አቶ ተስፋዬ በልጅጌ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ለማዳንና የምንፈልገውን የብልፅግና ትልም እውን ለማድረግ ትምህርትና እውቀት ዋነኛ መሳሪያችን ነው ሲሉ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የዘርፍ አስተባባሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ገለጹ።
የከፍተኛ ትምህርት ድጋፍና ክትትል አስተባባሪዎች የ2014 እቅድ ውይይት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።
አቶ ተስፋዬ “ወቅቱ ሁላችንም ኢትዮጵያን ከአደጋ ለመታደግ በተለየ የአርበኝነት ስሜት በጋራ መቆም ያለብን ወቅት ነው” ብለዋል።
ይህን ፈተና ተሻግረን ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ማማ ከፍ የማድረግ ትልቅ ሃገራዊ ትልምም ጎን ለጎን ማካሄድ አለብን ሲሉም ተናግረዋል።
ለእነዚህ ሁለት ትላልቅ ስራዎች ደግሞ ትምህርትና እውቀት ዋነኛ መሳሪያችን ናቸውም ነው ያሉት።
ወጣቱ በዚህ ውስጥ የተለየ ሚና እንዲጫወት፣ ለሃገሩ በተለየ ተቆርቋሪ እንዲሆን ማድረግም እኩል አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል።
ይህ እውን እንዲሆን ደግሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ከባቢ ሊኖር ይገባልም ነው ያሉት።
ለሁለት ቀን የሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ የእቅድ ትውውቅና የተሻሻሉ የአሰራር መመሪያ ላይ ወይይት እንደሚደረግ ከብልጽግና ፓርቲ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.