Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለመከላከያ ሰራዊት ከ31 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ31 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
የከተማ አስተዳደሩ ህዝቡን በማስተባበር 28 ሚሊየን ብር የገንዘብ እና ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ቁሳቁስ ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡
 
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ÷የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
የሚደረገው ድጋፍ የሀገርን ህልውና ለማስቀጠል ያለመ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ከመከላከያ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
 
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጃዋር በበኩላቸው÷ የተደረገው ድጋፍ ከማህበረሰቡ፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከአርሶ አደሩ እንዲሁም ከመንግስት ሰራተኛው የተሰበሰበ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
በቀጣይም በሚያስፈልገው ሁሉ ከመከላከያው ሰራዊት ጎን እንቆማለን ነው ያሉት፡፡
 
በቅድስት ተስፋዬ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.