Fana: At a Speed of Life!

በርካታ መጠን ያለው የብረት ክምችት ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 7 ለግንባታ አገልግሎት ሊውሉ የሚገባቸው የፌሮና ብረታ ብረቶች ክምችት ተያዘ፡፡

ብረታብረቶቹ የተያዙት የኢኮኖሚ አሻጥርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተዋቀረው ግብረ-ኃይል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአቃቂ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታምራት ሙሉጌታ÷ ብረቶቹ ለረጅም ጊዜ ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ የተከማቹና የተለያየ አይነትና መጠን ያላቸው በወቅቱ በገበያ ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ አሁን ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ሚና ይኖራቸው ነበር ብለዋል፡፡

በመዲናዋ እስካሁን በተደረገ ክትትልና ቁጥጥር እጅግ ከፍተኛ የሆነ የብረታ ብረት አይነቶችና በቢሊየን የሚገመት ዋጋ ያላቸውን የብረታ ብረት ውጤቶች መያዝ ተችሏል።

በተመሳሳይ በክፍለ ከተማው በግለሰብ ግቢ ውስጥ ተከማችተው የነበሩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ተይዘው፥ ለህብረተሰቡ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንዲሰራጭ መደረጉን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.