Fana: At a Speed of Life!

’ኦርጅናል ታይተን ጄል ጎልድ’’ የተባለው መድሃኒት ፈቃድ እንዳልተሰጠው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)‘’ኦርጅናል ታይተን ጄል ጎልድ’’ የተባለው መድሃኒት ፈቃድ እንዳልተሰጠው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር ባለሥልጣን ገለጸ፡፡

መድሃኒቱ በህገወጥ መንገድ ወደ ሃገር ዉስጥ ገብቶ በማህበራዊ ሚዲያ በመተዋወቅ ላይ እና በህገወጥ መንገድም በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ ተደርሶበታል፡፡

ይህ በጄል መልክ ተዘጋጅቶ በቆዳ ላይ በመቀባት ለውስን የጤና ዓላማ የሚውለው ጄል የቴስቶስትሮን ንጥረነገሮች የሚገኙበት መሆኑንም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

በዚህም በጥቂት መጠን በሐኪም ከሚፈቀደው በላይ ቆዳ ላይ ሲቀባ ከፍተኛ የቆዳ ቁስለትና እብጠትን፣ የሽንት ቱቦ ችግሮችን፣ በወንዶች ላይ የጡት እብጠትና ቁስለትን፣ ፈጣን የስሜት መለዋወጥንና የመንፈስ ጭንቀትን እንዲሁም የልብ ጤና ችግሮችን የሚያስከትል ነው ተብሏል፡፡

በመሆኑም በሐኪም ብቻ ሲታዘዝ ጥቅም ላይ መዋል ያለበት መድኃኒት መሆኑን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ህብረተሰቡም መድኃኒቱ በኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ባለሥልጣን ያልተመዘገበና በህጋዊ መንገድም ወደ ሃገር ውስጥ ያልገባ ስለሆነ ምርቱን ከመጠቀም እንዲቆጠብም አሳስቧል፡፡

ከዚህ ባለፈም ምርቱ ሲዘዋወር ሲገኝ በመስሪያ ቤቱ ነጻ የስልክ መስመር 8482 እና ለጸጥታ አካላት በመጠቆም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.