Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን ፈተናዎች በድል ተወጥታ የብልጽግና ጉዞዋን ታረጋግጣለች-አቶ ሙሳ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን ችግሮችና ጦርነት በድል ተወጥታ የብልጽግና ጉዞዋን ታረጋግጣለች ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ሙሳ አደም ተናገሩ።
የፓርቲው ጽህፈት ቤት የአመራር አባላትና ሠራተኞች በቢሾፍቱ ከተማ የችግኝ ተከላ በማካሄድ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
ስራ አስፈጻሚው አቶ ሙሳ አደም ኢትዮጵያዊያን አሸባሪውን የህወሓት ቡድንና ድህነትን ድል ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።
ምንም እንኳን አገሪቷ በጦርነትና በፈተናዎች ውስጥ ብትሆንም ሁሉንም በድል ተወጥታ የብልጽግና ጉዞዋን ታረጋግጣለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.