Fana: At a Speed of Life!

ኡጋንዳና ደቡብ ሱዳን የደህንነት ስጋት ያለበትን አውራ ጎዳና በጋራ ለመጠበቅ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡጋንዳና ደቡብ ሱዳን የደህንነት ስጋት ባለበት ከኒሙል እስከ ጁባ በተዘረጋው አውራ ጎዳና ላይ በጋራ ቅኝት ለማድረግና ለመጠበቅ ተስማሙ።

ሁለቱ ሀገራት ስምምነት ላይ የደረሱት የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች መንገደኞች ባልታወቁ ታጣቂዎች ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ነው፡፡

ስምምነቱ በየ10 ኪሎ ሜትሮች ላይ ፍተሻ ማድረግን እንደሚያካትት የኡጋንዳ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሬቤካ ካዳጋ ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት የምስራቅ አፍሪካ ሀገር አቋራጭ አሽከርካሪዎች ከፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ አድማ መምታታቸውንና ወደ 1 ሺህ የሚደርሱ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች በአውራ ጎዳናው ዋና መተላለፊያ ላይ መቆማቸው ነው የተገለፀው፡፡

በዚህ ዓመት ቢያንስ 30 ነጋዴዎች እና ከባድ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ሕይወት ማለፉን ዘገባው ያመላክታል።

የእርስ በእርስ ጦርነቱ ጋብ ያለላት ደቡብ ሱዳን ከጎረቤት ሀገራት በምታገኘው አስፈላጊ አቅርቦቶች ላይ ጥገኛ እንደሆነች የቢቢሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.