Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ገቢው በዋናነት ከውሃ ሽያጭና ከሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች የተሰበሰበ ነው ብሏል፡፡

ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ 1 ቢሊየን 389 ሚሊየን 19 ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 85 በመቶ ማሳካቱን ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ተጠቃሚዎች በወቅቱ የአገልግሎት ክፍያቸውን ያለመፈጸም የታየ ችግር ሲሆን÷ ባለስልጣኑ በበጀት አመቱ ለረጅም ጊዜ ውዝፋቸውን ያልከፈሉ ከ52 ሺህ በላይ ደንበኞች የውሃ አገልግሎት በማቋረጥ ከቅጣት ጋር ለመሰብሰብ መገደዱን ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.