Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለነፋስ መውጫ ሆስፒታል ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጉዳት ለደረሰበት የነፋስ መውጫ ሆስፒታል ድጋፍ እያደረጉ ነው።
በጎንደር እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች አስተባባሪነት 5 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ እና መድሃኒት በማሰባሰብ ዛሬ ለሆስፒታሉ ድጋፍ አድርገዋል።
ጅንካ፣ ወራቤ እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎች ያደረጉትን ድጋፍ ጨምሮ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ለነፋስ መውጫ ሆስፒታል ስራ ማስጀመሪያ አስረክበዋል።
በተመሳሳይ ዛሬ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ 600 መቶ ሺህ ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ እና መድሃኒት ድጋፍ አድርጓል።
የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ ፥ የህወሓት የሽብር ቡድን በላይ ጋይንት ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒልን ጨምሮ 14 የጤና ተቋማትን በመዝረፍ አውድሟል።
ህብረተሰቡ ከተጋረጠበት አደጋ በተጨማሪ አገልግሎት መስጫና የህክምናን ተቋማትን ጨምሮ ሌሎት መሰረተ ልማቶችን ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፥ ሆስፒታሉ የደረሰውን ጉዳት ጥናት ለማድረግ የባዮሜዲካል ባለሙያ ቡድኖችን በማስመጣት ጥናት እየተደረገ ነው።
በዛሬው ዕለትም ለወሊድ አገልግሎት የሚሆኑ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን እና ሆስፒታሉ ሙሉ በሙሉ ተጠናክሮ አገልግሎት መስጠት እስከሚችል ድረስ ድጋፉን እንደሚቀጥል የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አሸናፊ ታዘበው ተናግረዋል።
የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ክንዴ ገበየሁ በበኩላቸው፥ ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ድጋፍ መሰብሰቡን ገልጸዋል።
በምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.