Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ለ2ኛ ዙር መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ ለሁለተኛ ዙር መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ  አቶ ሞላ መልካሙ÷ለህልውና ዘመቻው ሃብት ከማሰባሰብ ጎን ለጎን በግንባር ሄደው የሚሳተፍና አካባቢያቸውን በንቃት የሚጠብቁ  ወጣቶች መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት በርካታ የከተማው ወጣቶች ወታደራዊ ስልጠና ወስደው መመረቃቸውን  ያስታወሱት ከንቲባው÷ተመራቂ  ወጣቶች አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ በሚደረገው ጥረት ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ  አሳስበዋል።

በተስፉፊው ህወሓት ቡድን የተከፈተው ጦርነት በድል እስኪጠናቀቅ ድረስም ብቃት ያላቸውን ወጣቶች የማሰልጠን ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

ተመራቂ ወጣቶች በበኩላቸው ኢትዮጵያን ከየትኛውም የጥፋት ሃይል ለመመከት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በአበራ መኮነን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.