Fana: At a Speed of Life!

ለቀጣይ 5 ዓመታት የሚበቃ የጨው ምርት መኖሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍዴራ የኢትዮጵያን ህዝብ ለቀጣይ 5 ዓመታት ሊመግብ የሚችል የምግብ ጨው ክምችት መኖሩን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
ሰሞኑን ተፈጥሮ የነበረው የጨው ዋጋ መጨመር ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
 
አፍዴራ ላይ ጨው ወደ መኪና ላይ በሚጭኑ ማህበራት የመጫኛ ዋጋ ይጨመርልን ጥያቄ በማንሳታቸው ጨው አምራች እና ጨው ወደ መኪና ላይ በሚጭኑ ማህበራት መካከል ጊዜያዊ አለመግባበት ተፈጥሮ ነበር፡፡
 
ይህን ተከትሎ ጨው ለአንድ ወር ሳይጫን በመቅረቱ ምክንያት በገበያ ውስጥ የጨው ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ እንደነበር ተመላክቷል፡፡
 
ሆኖም በአምራቾቹና በጫኞቹ መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት የተፈታ በመሆኑ በቂ የጨው ምርት ወደ ገበያ እየቀረበ ይገኛል፡፡
 
በአሁኑ ወቅት አፍዴራ ላይ 30 ሚሊየን ኩንታል የጨው ክምችት መኖሩን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡
 
የሀገሪቱ ወርሃዊ የጨው ፍጆታ 500 ሺህ ኩንታል መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ÷ በአፍዴራ የሚገኘው የጨው ክምችትም ለቀጣይ 5 ዓመታት ፍጆታ የሚበቃ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
 
አሁን ላይ በሀገሪቱ 6 ህጋዊ ጨው አምራች ፋብሪካዎች መኖራቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.