Fana: At a Speed of Life!

አኮቦ የወርቅ ማዕድን አምራች ድርጅት በኢትዮጵያ የሙከራ ፈቃድ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አኮቦ የተባለው የወርቅ ማዕድን አምራች ድርጅት በኢትዮጵያ በወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችለውን የሙከራ ፈቃድ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ ሰገሌ አካባቢ ባለው የወርቅ ቁፋሮ ፕሮጀክት ላይ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ማካሄድ የሚያስችለውን የሙከራ ኮንትራት ከኢትዮጵያ ማግኘቱን ገልጿል፡፡

ፒኮክ እና ሲምፕሰን ከተባሉ የዚምባብዌ ማዕድን ቁፋሮ ድርጅቶች ጋር በትብብር እንደሚሰራም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ የወርቅ ማዕድኑን ማውጣት የሚችልበትን የላቦራቶሪ ፍተሻ እያደረገ መሆኑንና ማዕድኑን ማውጣት የሚያስችሉ ውጤታማ ማሽነሪዎችን ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ-ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑንም ነው የገለጸው።

የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤቱ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደሚታወቅ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የውጤቱ መታወቅም ድርጅቱ ለሚያዘጋጀው የቅድመ-ምርት ጥናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ያስታወቁት የድርጅቱ ሀላፊ ጆርገን ኤቪየን÷ የቤተ-ሙከራ ውጤቱ እንደታወቀም ወዲያው ዲዛይኑን እንደሚያዘጋጅ ተናግረዋል፡፡

ፒኮክ እና ሲምፕሰን ድርጅቶች በአጋርነት የተመረጡት በአፍሪካ ውስጥ በዘርፉ ላይ ካላቸው የረዥም ጊዜ ልምድ በመነሳት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.