Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክንያታዊ ያልሆነ የምርት ዋጋ በመጨመር የኢኮኖሚ ጫና በመፍጠር የህዝብ ኑሮ እንዳይረጋጋ እያደረጉ ባሉ ነጋዴዎች እና ተቋማት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የደቡብ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ሒክማ ከይረዲን፥ 2013 በጀት ዓመት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ በኢትዮጵያ በተከፈተው ጦርነት ምክንያት የኢኮኖሚ መቃወስና የኢኮኖሚ አሻጥር የፈጠሩ 4 ሺህ 952 ነጋዴዎች የቃልና ጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።
ከዚህ ባለፈም 20 ሺህ 457 የንግድ ድርጅቶችን የማሸግ፣ 7 ሺህ 595 የንግድ ድርጅቶችን ማገድ፣ 22 ነጋዴዎች ባደረሱት ጥፋት ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ታይቶ ከስድስት ወር እስከ 2 ዓመት ተኩል የእስራት ውሳኔ እንዲበየንባቸው ተደርጓልም ነው ያሉት።
አሁን ላይ የሚታየውን የኢኮኖሚ አሻጥር በመፍጠር ሀገር ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር በተሳሳተ መንገድ ተባባሪ የሆኑ እንዲያርሙና ሆን ብለው አቅደውና አሲረው የሽብር ተግባርን የማስቀጠል ተግባር ላይ የተሰማሩት ላይ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ፣ ህጋዊነትን ለማስፈን በየደረጃው የሚገኙ አመራር እና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በቁርጠኝነት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በማቴዎስ ፈለቀ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.