Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ በበረራ ዘርፍ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ ዘርፍ የአፍሪካ መዳረሻ የሚያደርገውን ስትራቴጂክ ስምምነት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ተፈራረመ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቦይንግ ኩባንያ በዘርፉ የ70 ዓመታት የጋራ ታሪክ እንዳላቸው የጠቀሰው ወርልድ ኤርላይን ኒውስ ድረገጽ የመግባቢያ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ በሚል ማዕቀፍ ኢትዮጵያን የአፍሪካ አህጉር የአየር በረራ ማዕከል ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው ብሏል፡፡
ስምምነቱ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተና ዓለም አቀፍ የበረራ ደረጃን ያሟላ ትብብር የሚያመላክት ነው ተብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.