Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ሚኒስቴር ከሰባት ተቋማት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ከስድስት ሚኒስትር መስሪያ ቤቶችና ከንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር የሁለትዮሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
የመግባቢያ ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ከተቋማቱ ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር ተፈራርመዋል።
ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የግብርና ፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፣የጤና ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን፣ ንግድ ፣ የባህልናቱሪዝም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ናቸው።
የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቱ አዲሱን የስርአተ ትምህርት ሪፎሮም በቅንጅትና በትብብር በጋራ ለመተግበር ያለመ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.