Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ኤምባሲ ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን እና አይፓዶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡
በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሃብታሙ ሲሳይ÷ሁለቱ ሃገራት የቆየ ወዳጅነት እና ከ50 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው አውስተዋል፡፡
የቻይና ኤምባሲ ከዚህ በፊትም መጽሐፍትንና የኮቪድ-19 መከላከያ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በስጦታ ማበርከቱን እንዲሁም ለባለሙያዎች ተከታታይ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቻይና ኤምባሲ የባህል አታሼ ቺ ዥዋወይ በበኩላቸው÷በሁለቱ ወዳጅ ሃገራት መካከል የቆየ ግንኙነትና ትብብር እንዳለ አስታውሰው÷ ይህን ትብብር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.