Fana: At a Speed of Life!

የመተከል ዞን ሴቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ስንቅ አዘጋጁ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመተከል ዞን ሴት የመንግስት ሰራተኞች እና የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ስንቅ አዘጋጁ፡፡

የዞኑ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ እናትነሽ ማሩ ÷በዞኑ ውስጥ ሰላምን ለማስከበር ተሰማርቶ ለሚገኙ የሰራዊት አባላት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ከመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ጋር በመተባበር እየተከናወነ ያለው የስንቅ ዝግጅት ለሰራዊቱ ደጀን በመሆን አጋርነት የሚያሳይ እንደሆነ ሃላፊዋ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያን ለመበታተን ዓልሞ የተነሳውን አሸባሪ ሃይል ለማጥፋት በሚደረገው እንቅስቃሴ ሴቶች የሚጠበቅባቸውን ድርሻ በመወጣት የታሪክ አሻራቸውን አስቀመጠው ማለፍ እንዳለባቸውም ተገልጿል።

ሴቶቹ በበኩላቸው በቀጠናው ብሎም በሌሎች ግንባሮች ላይ ተሰማርቶ ለሚገኘው ሰራዊት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማድረግ ከመቼውም በላይ ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸውን ከመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.