Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት የትግራይ ወጣቶችን በሶስት ቀን ስልጠና ለጦርነት እየማገደ ነው-ምርኮኞች

አዲስ አበባ ፣ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሽብር ቡድኑ ህወሓት የትግራይ ወጣቶችን በሶስት ቀን ስልጠና ብቻ ለጦርነት እየማገደ መሆኑን በበርሃሌ ግንባር የተማረኩ ወጣቶች ተናገሩ፡፡

የህወሓት የሽብር ቡድን በአፋር ክልል ጥቃት ከከፈተባቸው አካባቢዎች የበረሃሌ ወረዳ አንዷ ናት፡፡

በዚህ ግንባር የአፋር ክልል ልዩ ሃይል፣ ፖሊስ እና ሚሊሻ ከህዝቡ ጋር በቅንጅት አሸባሪውን ህወሓት እየተፋለሙት ይገኛሉ፡፡

እስካሁን በተካሄደው ውጊያም የሽብር ቡድኑ በርካታ ቁሳዊ እና ሰብዓዊ ኪሳራ ያስተናገደ ሲሆን÷በዚህም በርካታ የቡድኑ አባላት እና የጦር መሳሪያዎች ተማርከዋል፡፡

በበርሃሌ ግንባር የተማረኩ ወጣቶች ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የሽብር ቡድኑ ህወሓት የትግራይ ወጣቶች እና ህጻናትን በሶስት ቀን ስልጠና ለጦርነት እየማገደ ነው ብለዋል፡፡

ትህነግ ወጣቶችን ለጦርነት ለመመልመል የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እንደሚጠቅምም ነው የተናገሩት፡፡

በሌላ በኩል የሽብር ቡድኑ ወጣቶችን ያለ ፍላጎት በማስገደድ ቤተሰቦቻቸው ሳያውቁ ለጦርነት እያሰማራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ሳቢያም በርካታ ወጣቶች እና ህጻናት ምክንያቱ ባልገባቸው ጦርነት ውድ ህይወታቸውን እያጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በጌታሰው የሺዋስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.