Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ወደ ጋና ያቀናል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ነገ ወደ ጋና ያቀናል፡፡
የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውብቱ አባተ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና ብሔራዊ ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ጋና ከቡድኑ ጋር የሚጓዙ የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል፡፡
ዋልያዎቹ ጨዋታቸውን ነሐሴ 28 ቀን ያደርጋሉም ነው የተባለው፡፡

በሌላ መርሃ ግብር ጳጉሜን 3 ቀን 2013 ዓ.ም በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ከዚምባብዌ ጋር እንደሚያደርጉ ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.