Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሽብር ድርጊት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 284 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባን የሽብር ቀጠና ለማድረግ የአሸባሪው ህወሓት ቡድንን ዓላማ ለማሳካት ተንቀሳቅሰዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 284 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።
199 ሽጉጥ ከ2 ሺህ 453 ጥይት ጋር፣ 32 ክላሽንኮቭ 5 ሺህ ከሚልቅ ጥይት ጋር እንዲሁም 4 የጦር ሜዳ መነፅር ከተጠርጣሪዎቹ እጅ፣ ከስራ ቦታቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው መያዝ መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ለአሸባሪው ህወሓት ሃገር የማፍረስ ተልዕኮ የገቢ ምንጭ ሆኖ እንዲያገለግል ያከማቹት ከአንድ ኪሎ ተኩል በላይ ወርቅ እንዲሁም 37 ሺህ 294 ነጥብ 8 ግራም የብር ጌጣጌጥ መያዙን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ ለሽብር ተግባር የሚጠቀሙባቸው የአዲስ አበባ ፌዴራል ፖሊስ፣ የመከላከያ ሠራዊት፣ የማረሚያ ቤትና የራሱ የህወሓት የሽብር ቡድን አልባሳት መያዛቸውንም አስረድተዋል።
በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ 123 የምርመራ መዝገብ መደራጀቱንም ነው የገለጹት።
የጥፋት ቡድኑ የትኛውንም ዓይነት ሽብር ከመፈፀም ስለማይቦዝን ህብረተሰቡ አካባቢውን ከመጠበቅ ባለፈ መረጃ በመስጠት ከፖሊስ ጋር የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.