Fana: At a Speed of Life!

የገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የጉሙሩክ ኮሚሽን እና ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አመራሮችና ሰራተኞች በሶማሌ ክልል ጉርሱም ወረዳ ቦምባስ ከተማ የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት እና ተያያዥ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡
በዚህም የ10 አቅመ ደካማ ቤትን ለማደስ የሚያስችል 1 ሚሊየን 50 ሺህ ብር እና 25 ሚሊየን ብር የሚገመት ምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጥ በክልሉ ለሚኖሩ አቅመ ደካሞች አበርክተዋል፡፡
ድጋፉን ለሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ያስረከቡት የጉምሩክ ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ÷ ሀገራችን ከውስጥም ከውጭም በርካታ ፈታና ቢገጥማትም ኮሚሽኑ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከክልሉ ህዝብ ጋር በመተባበር ኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር እስከሚወገዱ ድረስ በትብብር እንሰራለን ብለዋል፡፡
የተጠሪ ተቋማቱ ለክልሉ ህዝብ ድጋፍ ሲያደርጉ ይሄኛው የመጀመሪያ አለመሆኑን ድጋፉን የተቀበሉት የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ገልፀዋል፡፡
በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋናቸውን አቅርበው ለወደፊትም በትብብር ለመስራት ቃል መግባታቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.