Fana: At a Speed of Life!

ከከሚሴ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ 53 ጩቤ እና ሌሎች ሕገወጥ ቁሳቁስ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከከሚሴ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ የነበረ ጩቤ፣ የጥይት መያዣ ካርታ እና ሌሎች ሕገወጥ ቁሳቁስ በዛሬው እለት መያዛቸውን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

53 ሕገወጥ ጩቤ፣ 30 የጥይት መያዣ ካርታ፣ 30 እንግብ፣ 30 የትጥቅ መያዣ ቀበቶ እንዲሁም 3 ኪሎ የሚመዝን አደገኛ እጽ መሰል ነገር ከከሚሴ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል በፖሊስ እና በማህበረሰቡ ትብብር መያዙንጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

ሕገወጥ ቁሳቁሱን ሲያዘዋውር የነበረው ግለሰብም ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.