Fana: At a Speed of Life!

ሀገር የህልውና ዘመቻ ላይ እያለች ህዝብን ችግር ላይ መጣል ተቀባይነት የለውም- የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የዋጋ ንረትና የኢኮኖሚ አሻጥርን መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ከአስመጪዎች፣ ከሸማቾች የመብት ጥበቃ ማህበራት፣ ከአምራቾች፣ ከሕብረት ስራ ማህበራትና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይቷል።
በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የውስጥ እና የውጭ ሃይሎች ለግል ጥቅማቸው እየተሯሯጡና በዋጋ ጭማሪ፣ ምርት በማከማቸትና በገበያው ላይ እጥረት በመፍጠር እንዲሁም በሌሎች ህገ-ወጥ ተግባራት ላይ በመሳተፍ የኢኮኖሚ አሻጥር በመስራት ህብረተሰቡን በማማረር ሀገርን ለማፍረስና እየሰሩ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል፡፡
የሀገርን ሉአላዊነት አስጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ በሚደረገው ጥረትም እንደ ወትሮው ሁሉ አንድነትን ማጠናከርና ለህልውና ዘመቻው በጋራ መቆም እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡
የንግዱ ማህበረሰብ አካላት በበኩላቸው እያንዳንዱ አምራችና ሸማች የኢኮኖሚ አሻጥሩን በመከላከል የኑሮ ውድነቱን መታገል አለበት ብለዋል።
መንግስት የኢኮኖሚ አሻጥር በሚፈፅሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይገባልም ነው ያሉት፡፡
ከህግ ማስከበሩ ጋር በተያያዘ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የተገኙ 50 ሺህ 450 የንግድ ድርጅቶች እንደታሸጉ እና 1 ሺህ 520 የሚሆኑት ደግሞ ፈቃዳቸው ተሰርዟል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም 257 የሚሆኑ የንግድ ድጅቶች ላይ እገዳ ሲጣል፣ 80 ሺ 641 ያህል የንግድ ድርጅቶች ላይ ደግሞ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውና 2 ሺህ 230 ያህሉ የንግድ ተቋማት ደግሞ ክስ እንደተመሰረተባቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.