Fana: At a Speed of Life!

ሁለት ልጆቻቸውን ለህልውና ዘመቻ መርቀው የሸኙት አባት

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ መንግስቱ ንጉሴ የ70 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ እና የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ነዋሪ ናቸው።
ሁለት ልጆቻቸው የህልውና ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ መርቀው መሸኘታቸውን የሚናገሩት አቶ መንግስቱ የአሁኑ ትውልድ የአባቶቹን የአሸናፊነት መንፈስ ተላብሶ የሃገሩን ህልውና ማስጠበቅ እንዳለበት ገልጸዋል።
ለሀገሬ ከሆነ ልጆቼን መርቄ በመሸኘት ሳልወሰን እሰፈላጊ ከሆነ እኔ ራሴ ለመዝመት ዝግጁ ነኝ ብለዋል።
ወጣቶች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ለህልውና ዘመቻው ዝግጁ መሆን አለበት ነው ያሉት።
አሸባሪው ህወሓት የኢትዮጵያውያንን የአብሮነት እሴት ለዓመታት ሲሸረሽር መቆየቱን የገለጹት አቶ መንግስቱ፤ የሽብር ቡድኑን ሙከራ በተባበረ ክንድ መመከት ይገባል ብለዋል።
እንደ አቶ መንግስቱ ሁሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ነዋሪዎች የሀገር ሽማግሌዎች የኢትዮጵያን ህልውና ማስጠበቅ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ይናገራሉ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.