Fana: At a Speed of Life!

የአፋር ክልል ምክር ቤት 8 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ለ2014 የሥራ ዘመን ማስፈጸሚያ 8 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በጀት አጸደቀ።
የክልሉ ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ዛሬ በጀቱን ያጸደቀው በቀረበው ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ነው።
የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ሐሰን ለምክር ቤቱ እንዳብራሩት÷ በጀቱ ከፌደራል መንግሥት ድጎማ ፣ ከውጭ እርዳታና ከክልሉ የውስጥ ገቢ ታሳቢ ተደርጎ ተዘጋጅቷል።
በጀቱ የክልሉን የጤናና ውሃ ችግሮችን ለማቃለል እንዲሁም የሰላምና ጸጥታ ተቋማትን ለማጠናከር ትኩረት ማድረጉም ተመልክቷል።
በየደረጃው ለሚገኙ የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚዎች ለመደበኛና ካፒታል በጀት እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያም እንደሚውል መገለጹንም ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.