Fana: At a Speed of Life!

የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች በለንደን፣ በርሚንግሃም እና ኮቨንተሪ ተካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያን ለማዳን ከመከላከያና ከህዝባዊ ሀይል ጎን በመቆም ድርሻዬን እወጣለሁ” በሚል የሀገርን ሕልውና እየጠበቀ ላለው መከላከያ ሠራዊትና ህዝባዊ ሀይል ድጋፍ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፓርክ ላይ ተካሄደ፡፡

በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲና የ”Defend Ethiopia” የዩናይትድ ኪንግደም ግብረሀይል በጋራ በመተባበር ባዘጋጁት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል፡፡

በገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ ላይ የተገኙት በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ዝግጅቱ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ምክንያት ከሀገር ቢወጡም ኢትዮጵያ ከውስጣቸው እንደማትወጣ ዳግም ያረጋገጠ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሃገር ቤት ያለው መላው ህዝብ ከመንግስት ጎን በመቆም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪው ህወሓትን ለመደምሰስ እየተፋለመ መሆኑን አንስተው በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም በገንዘብ በመደገፍ እንዲሁም በሀገሪቱ ያለውን ተጨባጭ እውነታ ለዓለም በማሳወቅ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የ”Defend Ethiopia” የዩናይትድ ኪንግደም ግብረሀይል አስተባባሪ አቶ ዘላለም ተሰማ በበኩላቸው “እኛ ረግጠን እስካልገዛናት ድረስ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እስከ ሲኦል እንወርዳለን ያለውን የሽብርተኛውን ቡድን አመራሮች በሚወርዱበት ሲኦል ውስጥ እንዲቀሩ የማድረግ ኃላፊነት የመከላከያ ሠራዊትና ህዝባዊ ሀይሉ ብቻ ሳይሆን የእኛ ጭምር ነው” ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.