Fana: At a Speed of Life!

በመጪው የትምህርት ዘመን የሚተገበረው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ከ2014 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ገቢራዊ የሚደረገው አዲሱን የአጠቃላይ ትምህርት ፍኖተ ካርታ ሰነድ ይፋ አደረገ።

ከ26 ዓመታት በፊት ጀምሮ በየአምስት ዓመቱ የስርዓተ ትምህርት ክለሳ የሚደረግ ሲሆን ለስድስተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የአጠቃላይ ትምህርት ፍኖተ ካርታም ከ2014 ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ይተገበራል።

ነባሩ ስርዓተ ትምህርት የጥራትና አግባብነት እንዲሁም የሰው ሀብት ስብዕና ግንባታ ጉድለቶች እንደነበሩበት ተወስቷል።

በስርዓተ ትምህርቱ ከገበያው ፍላጎት ጋር አለመጣጣም፣ የመምህራን ብቃት ማነስ፣ በቴክኖሎጂ አለመደገፍና ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነት ሌሎች የዘርፉ ቁልፍ ችግሮች እንደነበሩ ተነስቷል።

ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርትን ያጠቃለለው የአጠቃላይ ትምህርት ፍኖተ ካርታ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያስችላሉ የተባሉ ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎችን ማካተቱም ተገልጿል።

የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ ብሔራዊ አንድነትና ብዝሃነት፣ ጥራት ማሻሻያና የስራ ገበያ፣ ተደራሸነትና ፍትሃዊነት፣ ወጣቶችና ጎልማሶች ትምህርትና የሙያ ብቃት ማረጋጋጫ የፍኖተ ካርታው ፕሮግራሞች ናቸው።

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ግብረ ገብነት፣ ሃገር በቀል እውቀት፣ ሙያና የቀለም ትምህርት፣ ቴክኖሎጂ፣ ምርትና ተግባር፣ ጥናትና ምርምር ትኩረት የተደረገባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በጉባዔው ትምህርት ሚኒስቴር ከስድስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ከክልል ትምህርት ቢሮዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.