Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ሶስተኛው ማዕበል በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ካለፉት ስምንት ሳምንታት ወዲህ በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሶስተኛ ማዕበል በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምላሽ አስተባባሪ አቶ መብራቱ ማሴቦ÷ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ሶስተኛ ማዕበል ላለፉት ስምንት ሳምንታት በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መምጣቱን ተናግረዋል።

የወረርሽኙ ማዕበል በተለይ ደግሞ ከሀምሌ ወር የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ጀምሮ መጠነኛ መቀነስ አሳይቶ እንደነበረ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ሆኖም በነሐሴ ወር እንደ አዲስ ማገርሸቱንና በዚህም ከ600 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ አስተባባሪው ጠቁመዋል።

በአንድ ቀን ምርመራ ብቻ እስከ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው እየታወቀ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በቫይረሱ የተያዙ፣ ምልክቱን ያላሳዩ፣ ያልተመረመሩ በርካታ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉና የምርመራ አቅም ውስንነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችልም አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.