Fana: At a Speed of Life!

ታሪካዊው የጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በአሸባሪው ቡድን ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታሪካዊው የጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት።

የፈለገ ፀሐይ በቅሎ አግት ጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በሦስተኛው ክፍለዘመን እንደተመሰረተ ይገለጻል።

መሪጌታ አብራራው መለሰ ጨጨሆ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል ገዳም ገንዘብ ያዥ ናቸው።

ትናንት ምሽት አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን በከባድ መሳሪያ ጥቃት ቤተክርስቲያኑን ማውደሙን ተናግረዋል።

መሪጌታ አብራራው የሽብር ቡድኑ በእምነት ተቋማት ላይ ይህን መሰል ውድመት ማካሄዱ ለጸረ ሕዝባዊነቱ ማረጋገጫ ነው ብለዋል።

“እያጠፋናችሁ ነው የምንሄደው ብለው ነበር፤ እንዳሉትም አድርገዋል” ነው ያሉት።

አሸባሪው ቡድን ባደረሰው የከባድ መሳሪያ ጥቃት የቤተክርስቲያኑ 14 መስኮቶች፣ 5 በራፎች፣ ሕንጻውና ጣሪያው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ብለዋል።

መሪጌታ አብራራው የሽብር ቡድኑ በግቢው ውስጥ የሚገኙ ዕጽዋትንም እንዳወደመ ተናግረዋል።

የገዳሙ ፍልፍል ዋሻም በአሸባሪ ቡድኑ መፍረሱን ጠቁመዋል።

ቤተክርስቲያኑ ወደነበረበት እንዲመለስ ርብርብ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

“በአካባቢው ሆነው ቤተክርስቲያኑን ያስመቱ ግለሰቦችም በጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል” ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.