Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በጋይንት የሶስት ህፃናት ወላጆችን በግፍ ረሽኗል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በጋይንት የሶስት ህፃናት ወላጆችን በግፍ መረሸኑ ተገለጸ፡፡
ሟች ደሴ ጌታው እና ገነት አለባቸው የሶስት ወንድ ልጆች ወላጆች ሲሆኑ÷ የነፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪ ናቸው።
አሸባሪው ቡድን እናት እና አባትን የሟች ደሴ አባትን እና የስምንት ዓመት የወንድሙን ልጅ በአጠቃላይ አራት የቤተሰብ አባላትን ምግብ እየተመገቡ ባሉበት በግፍ እንደገደላቸው የሟቾቹ ቤተሰቦች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል፡፡
እናት እና አባት ሲገደሉ አብሮ የነበረው የሁለት ዓመት ከስድስት ወር ህፃን በእናቱና አባቱ አስከሬን መሀል በህይወት ተገኝቷል።
ከነፋስ መውጫ 12 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው መሸለሚያ አቦ ነው ሟቾቹ በግፍ የተረሸኑት።
የሟች ገነት አባት አቶ አለባቸው መብሬ ‘‘አሸባሪው ህወሓት ቤተሰቤን በጭካኔ ገድሎብኛል፤ የልጅ ልጆቸን ያለ እናት አባት አስቀርቶብኛል’’ ሲሉ የደረሰባቸውን መሪር ሀዘን ተናግረዋል።
የሟቾቹ ልጆች የዘጠኝ፣ ሰባት እና ሁለት ዓመት ከስድስት ወር እድሜ ላይ ሲሆኑ÷ የሚደግፋቸው እና የሚያስተምራቸው ወገን ይፈልጋሉ።
በዙፋን ካሳሁን እና ምንይችል አዘዘው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.