Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ አፍሪካ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ አፍሪካ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያን ማግኘቷን አስታወቀች፡፡

ተመራማሪዎች ሲ.1.2 በተባለው አዲስ ዝርያ ላይ ክትትል እያደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል።

አዲሱ የቫይረሱ ዝርያ ከደቡብ አፍሪካ በተጨማሪ በሰባት የአፍሪካ ሃገራት ፣ በእስያ ፣ በአውሮፓ እና በኦሺኒያ ታይቷልም ነው የተባለው፡፡

ተመራማሪዎችም የአዲሱን ዝርያ ባህሪና ሁኔታ እያጠኑ ነው ተብሏል፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ የቴክኒክ መሪ ማሪያ ቫን ከርክሆቭ ዝርያው እየተሰራጨ አይመስልም ብለዋል።

የዴልታ ዝርያ አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ በመሰራጨት ቀዳሚ ነው ያሉት ሃላፊዋ አዲሱ ዝርያ የሚሰራጭ ከሆነ የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚያሳውቅ ተናግረዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ 2 ሚሊየን 770 ሺህ 575 ሰዎች ሲያዙ 81 ሺህ 830 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.