Fana: At a Speed of Life!

አቶ አገኘሁ ተሻገር ከዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ከተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ አዴል ክኾድር ጋር ተወያይተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት÷ ዩኒሴፍ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተፈናቅለው በቻግኒ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ወገኖችን በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

አሸባሪው እና ወራሪው የትህነግ ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች በከፈተው ጦርነት በርካታ ዜጎች መገደላቸውን እና በርካቶች መፈናቀላቸውን ለተወካይዋ ገለፃ አድርገውላቸዋል።

አሸባሪው ቡድን በፈጸመው ወረራ ሕፃናት፣ ሴቶች እና አረጋውያን የከፋ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን እና በርካታ የትምህርት እና የጤና መሠረተ ልማቶች መዘረፋቸውንም ጨምረው አብራርተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የህወሓት የሽብር ቡድን ወረራ በፈፀመባቸው በሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም ዋግኸምራና ሰሜን ወሎ ዞኖች ግማሽ ሚሊየን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን÷ 4ሚሊየን ደግሞ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች ማህበራዊ ተቋማት በተለይም ትምህርት ቤቶች እና ጤና ተቋማትን አውድሟል፤ ዜጎች ላይ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መፈፀሙን ገልፀዋል።

በዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ አዴል ክኾድር በአፋር እና አማራ ክልሎች ተፈናቃዮችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ገልጸው÷ ዩኒሴፍ ለተፈናቃዮች አፋጣኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ እንደሚሠራ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.