Fana: At a Speed of Life!

በመድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የሀዋሳ ማዕከል በካይዘን አተገባበር በአፍሪካ ደረጃ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የሀዋሳ ማዕከል በካይዘን አተገባበር በአፍሪካ ደረጃ አሸናፊ መሆኑ ለሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
በኤጀንሲው ስር በሀገር አቀፍ ደረጃ 18 ቅርንጫፎች እንዳሉ በመጥቀስ የሀዋሳው ማዕከል በካይዘን አተገባበርም ሆነ በስራ አፈጻጸሙ ከቀዳሚዎች ተርታይገኛል ብለዋል፡፡
ብክነትን ለመቀነስና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የካይዘን ፍልስፍና አወንታዊ ሚና ያለው በመሆኑ፥ ከሀዋሳው ቅርንጫፍ ትምህርት መቅሰም እንደሚገባ ተናግረዋል።
በኤጀንሲው የሀዋሳ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅና የደቡብ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ዘመንለገሰ በበኩላቸው፥ ቅርንጫፉ ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ደረጃ አሸናፊ በመሆኑ ደስታቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም የስራ ጥራትና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያነሳሳ መናገራቸውን ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቨዥን ድርጅት ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.