Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻ የሚውል ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሥራት ዓፀደወይን ተቋሙ በ2013 ዓ.ም ከመማር ማስተማሩ በተጓዳኝ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ መልካምና አበረታች ስራዎች መስራቱን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ለህልውና ዘመቻ እንዲውል ወስነዋል፡፡

ሰራተኞቹ ድጋፉን ያደረጉት “ከህልውና የሚቀድም የለም” በሚል መንፈስ መሆኑን ዶክተር አሥራት መግለፃቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች በ”ህግ ማስከበር” ወቅትም ከ4 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ “ሰብዓዊ ድጋፍ” ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.