Fana: At a Speed of Life!

ሕብረቱ ከአሜሪካ ወደ አውሮፓ የሚደረግ ጉዞ እንዲታገድ ምክረ- ሐሳብ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ እየተባባሰ በመጣው የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከአሜሪካ ወደ አውሮፓ ሕብረት አባል ሀገራት የሚደረግ ማንኛውም ጉዞ እንዲታገድ የአውሮፓ ሕብረት ምክር ቤት ምክረ-ሃሳብ አቀረበ፡፡

ምክር ቤቱ ያሳላለፈው ውሳኔ ለሰኔ የበጋ በዓላት አሜሪካ ከደህንነት ስጋት ነፃ ስለመሆኗ ያሳለፈውን ውሳኔ የቀለበሰ ነው ተብሏል፡፡

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ባለፉት ሳምንታት በአሜሪካ 977 ሺህ 947 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ እና 7 ሺህ 394 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።

ምክር ቤቱ ከአሜሪካ በተጨማሪ ወደ እስራኤል፣ ሊባኖስ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ሜቄዶንያ እና ኮሶቮ የሚደረግ ጉዞ አስፈላጊ እንዳልሆነም ነው የገለፀው፡፡

ምክረ-ሃሳቡ ግዴታ የሚጥል እንዳልሆነና ገደብ ከተጣለባቸው ሀገራት ወደ ሕብረቱ ጉዞ በሚያደርጉ መንገደኞች ላይ ግን በለይቶ ማቆያ መቆየትን ጨምሮ ጥብቅ ምርመራ እና ክትትል እንደሚካሄድባቸው ነው የገለፀው፡፡

ምንጭ፦ ሺንዋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.